ከሆስፒታል ውጭ ይቆዩ፣ ከልጅ ልጆችዎ ጋር አብረው ይቆዩ።
እያንዳንዱ ዕድሜው ከስድስት ወራት እና ከዚያ በላይ የሆነው ሰው የ2024 የመኸር ወቅት የCOVID ክትባትን ከኢንፍሉዌንዛ ክትባት ጋር ስለመውሰድ ማሰብ አለበት። ዕድሜዎ 50 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ስለክትባቶቹ ጥቅሞች አጥብቀዉ ማሰብ አለበዎት። በሆስፒታል ውስጥ መቆየት የበዓል ወቅት ዕቅዶችዎ አካል እንዲሆን አይፍቀዱ።
ሰዎች ዕድሜያቸው ዕየገፋ ሲሄድ የበሽታ መከላከል አቅማቸዉ እየተዳከመ ይሄዳል። በእድሜ የገፉ አዋቂ ሰዎች በተጨማሪም ሌሎች የጤና እክሎች ሊኖሩባቸዉ ይችላል። እንደ አስም እና የስኳር በሽታ የመሳሰሉ የጤና እክሎች ያሉባቸው ሰዎች ከባድ ምልክቶች የማየት ወይም በመጨረሻም ወደ ሆስፒታል የመግባት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
ከልጅ ልጆችዎ ጋር የሚኖሩዎት ትውስታዎች አያምልጡዎ። ክትባት ከቤተሰብዎ እና ከአዝናኝ ተግባሮችዎ ጋር አብረው እንዲቀጥሉ በሽታ ይከላከልለዎታል። የልጅ ልጆችዎን እድገት ለማየት አጠገባቸው መቆየትዎን ያረጋግጡ። የልጅ ልጆችዎ የእርስዎ አጠገባቸው መኖር ያስደስታቸዋል።
የCOVID ክትባት እስከ መጨረሻው የሚዘልቅ አይደለም። የCOVID ክትባት ከአንዳንድ ሌሎች ክትባቶች የሚለይበት መንገድ ይህ ነው። በጊዜ ሂደት ሰውነትዎ ከCOVID ክትባት ያገኛቸውን የመከላከል አቅም ይዘነጋል። ሰውነትዎን ያስታውሱት።
COVID በተጨማሪም በጊዜ ሂደት ይቀያየራል። ከብዙ ዓመታት በፊት የወሰዱት ክትባት አሁን አይከላከልለዎትም። በተጨማሪም የCOVID ቫይረስ በሚችለው መጠን ብዙ ሰዎችን ማጥቃት ስለሚፈልግ እራሱን ይቀያይራል። ወቅታዊ ክትባት መውሰድ የበሽታ መከላከያ ስርዓትዎ ቫይረሱ እራሱን ሲቀያይር ለመከላከል መዘጋጀቱን ለማረጋገጥ ይረዳዎታል።
የኢንፍሉዌንዛ ክትባት መውሰድ ሌላ የመከላከል ደረጃ ይጨምራል። በተጨማሪም ዕድሜያቸው 65 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ አዋቂዎች የኢንፍሉዌንዛ ክትባትን ከፍተኛ መጠን እንዲወስዱ ይመከራል። ይህ ጠንካራ የበሽታ መከላከያ ምላሽ ይሰጥዎታል። ሆኖም የትኛውም የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ምንም የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ካለመውሰድ የተሻለ ነው። ከፍተኛ መጠን ያለው ክትባት ማግኘት ካልቻሉ አይጠብቁ።
የCOVID ክትባቶች የአዲስ ክትባቶች መደበኛ የምርመራ ሂደትን ከማለፋቸውም በተጨማሪ የትኛውም መደበኛ ደረጃዎች አልተዘለሉም። እንደ የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ሁሉ የCOVID ክትባቶች የሙከራ አይደሉም። ክትባቶቹ ለአስር ዓመት በተጠና ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ክትባቶቹ ለጥናቶቹ ፍቃደኛ በሆኑ ሰዎች ላይ በጥንቃቄ ተሞክረዋል። ከዚያም በኋላ በመላው ዓለም የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ተመራማሪዎችና ጥናቶች ክትባቱ ምን ያክል ጠቃሚና አስተማማኝ እንደሆነ አረጋግጠዋል። ክትባቱ ለከባድ ህመሞችና ሊያጋጥሙ ለሚችሉ የረጅም ጊዜ ችግሮች ተጨማሪ የመከላከያ ደረጃ እንደሆነ ተረጋግጧል። በወረርሽኙ ወቅት ውጤታማ ክትባት ማዘጋጀት መቻሉ ታሪካዊ ስኬት ነው። ክትባቱ ብዙ ህይወት ታድጓል።
አብዛኞቹ ክትባቶች እንደ ድካም ወይም የእጅ መዛል የመሳሰሉ የአጭር ጊዜ የጎኒዮሽ የጤና ችግሮች አሏቸው። አነስተኛ የክትባት የጎኒዮሽ ውጤቶች ማለት ሰውነትዎ ከቫይረሶቹ እራሱን እየተከላከለ እንደሆነ ያሳያል።
በሌላ በኩል ደግሞ በCOVID ወይም በኢንፍሌንዛ በመታመም ምክንያት የሚታዩ ምልክቶች የበለጠ ከባድ ናቸው። በCOVID ወይም በኢንፍሌንዛ ምክንያት መታመም በጉንፋን ከመታመም ይለያል። ትንሽ ህመም ወደ ሆስፒታል ከመሄድ ይሻላል።
ክትባቱን በመውሰድ ምክንያት ከባድ የጤና እክሎች የሚያጋጥሙት አልፎ አልፎ ነው።
ክትባቱን በመውሰድ ምክንያት በልብ በሽታ የመያዝ እድልዎ በCOVID ምክንያት ከመያዝ እድልዎ ያነሰ ነው። በCOVID ምክንያት በመታመም እና ክትባቱን በመውሰድ መካከል ያለው አንዱ ዋነኛ ልዩነት በCOVID መያዝ የሚያስከትላቸው የረጅም ጊዜ ችግሮች የማይታወቁ መሆኑ ነው።
ጤናማ ቢሆኑም እንኳ ህይወትዎ በCOVID እና ኢንፍሉዌንዛ የተነሳ ሊፋለስ ይችላል። በተለይም በሚከተሉት ሁኔታዎች የCOVID ክትባት መውሰድዎ አስፈላጊ ነው:
- ዕድሜዎ 65 ዓመት እና ከዚያ በላይ ከሆነ
- በረጅም ጊዜ የእንክብካቤ ተቋም ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ወይም አካል ጉዳተኛ ከሆኑ።
- እንደ መሰላቸትና ጭንቀት የመሳሰሉ የአእምሮ ጤና እክሎች ካሉብዎ
- ክብደትዎ ከመጠን በላይ ከሆነ
- የጤና እንክብካቤ ተደራሽነትዎ ውሱን ከሆነ
የወንበር ቀበቶ ያደርጋሉ፣ አይደለም እን?
ጤናማ ሆነው መቆየትዎ እና ወቅታዊ የCOVID ክትባት የማያስፈልግዎ መሆኑ በጣም ጠንካራ ስለሆኑ ቀበቶ አያስፈልግዎትም እንደማለት ነው። ሁለቱም ሊተነበዩ በማይችሉ ሁኔታዎች ወቅት እርስዎን እና የሚወዷቸውን ሰዎች ለመከላከል የተዘጋጁ የመከላከያ እርምጃዎች ናቸው። ጥቂት ታሪክ: የወንበር ቀበቶ መጀመሪያ በመጣበት ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት የነበረ ቢሆንም አሁን የዕለት ከዕለት አኗኗራችን አካል ሆኗል። ምንም ያክል ጠንካራ ቢሆኑም እንኳ ቫይረሱ ከመቀያየር በተጨማሪ ጤናማ ሰዎችን እንዲታመሙ ሊያደርግ ይችላል። ይህ ቀደም ሲል በCOVID ታመው ቢሆንም እንኳ ይሰራል።
የCOVID የሚችለውን ያክል ብዙ ሰዎችን ለማጥቃት እራሱን ይቀይራል። ወቅታዊ ክትባት መውሰድ የበሽታ መከላከያ ስርዓትዎ ቫይረሱን እራሱን ሲቀይር ለመከላከል መዘጋጀቱን ለማረጋገጥ ይረዳዎታል።
ለስራዬ ስል ክትባቱን ወስጃለሁ። በድጋሚ የሚያስፈልገኝ ለምንድን ነው? ክትባቱ የስራ መስፈርት ሳይሆን ጤናዎን ስለመጠበቅ እና በህመም ምክንያት የእረፍት ቀናት እንዳይወስዱ ስለማድረግ ነው። በተጨማሪም ካልታመሙ በሽታውን ወደ ሌሎች ሰዎች አያስተላልፉም።
የCOVID ክትባቶች የአዲስ ክትባቶች መደበኛ የምርመራ ሂደትን ከማለፋቸውም በተጨማሪ የትኛውም መደበኛ ደረጃዎች አልተዘለሉም። ልክ እንደ ኢንፍሉዌንዛ ክትባት ሁሉ የCOVID ክትባት ሙከራ አይደለም። ክትባቶቹ ለአስር ዓመት በተጠና ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ክትባቶቹ ለጥናቶቹ ፍቃደኛ በሆኑ ሰዎች ላይ በጥንቃቄ ተሞክረዋል። ክትባቱ በሺዎች በሚቆጠሩ ተመራማሪዎች ተሞክሯል። ክትባቱ ለከባድ ህመሞችና ሊያጋጥሙ ለሚችሉ የረጅም ጊዜ ችግሮች ተጨማሪ የመከላከያ ደረጃ እንደሆነ ተረጋግጧል። በወረርሽኙ ወቅት ውጤታማ ክትባት ማዘጋጀት መቻሉ ታሪካዊ ስኬት ነው። ክትባቱ ብዙ ህይወት ታድጓል።
አብዛኞቹ ክትባቶች እንደ ድካም ወይም የእጅ መዛል የመሳሰሉ የአጭር ጊዜ የጎኒዮሽ ችግሮች አሏቸው። አነስተኛ የክትባት የጎኒዮሽ የጤና ችግሮች ማለት ሰውነትዎ ከቫይረሶቹ እራሱን እየተከላከለ እንደሆነ ያሳያል።
በሌላ በኩል በCOVID ወይም ኢንፍሉዌንዛ በመታመም ምክንያት የሚታዩ ምልክቶች የበለጠ ከባድ ናቸው። በCOVID ወይም ኢንፍሉዌንዛ ምክንያት መታመም በጉንፋን ከመታመም የተለየ ነው። ትንሽ ህመም ወደ ሆስፒታል ከመሄድ የተሻለ ነው።
ክትባቱን በመውሰድ ምክንያት ከባድ የጤና ችግሮች የሚያጋጥሙት አልፎ አልፎ ነው።
ክትባቱን በመውሰድ ምክንያት በልብ በሽታ የመያዝ እድልዎ በCOVID ምክንያት ከመያዝ እድልዎ ያነሰ ነው። በCOVID ምክንያት በመታመም እና ክትባቱን በመውሰድ መካከል ያለው አንዱ ዋነኛ ልዩነት በCOVID መያዝ የሚያስከትላቸው የረጅም ጊዜ ተጽእኖዎች የማይታወቁ መሆኑ ነው።
ጠንካራ መሆንዎና የበሽታ መከላከል አቅምዎ ከፍተኛ ነው ማለት የመታመም ስጋት የለብዎትም ማለት አይደለም። ጤናማ ቢሆኑም እንኳ ህይወትዎ በCOVID እና ኢንፍሉዌንዛ የተነሳ ሊፋለስ ይችላል። በተጨማሪም በሚከተሉት ሁኔታዎች በCOVID በከባድ ሁኔታ የመታመም እድልዎ ከፍተኛ ነው:
- እንደ መሰላቸትና ጭንቀት የመሳሰሉ የአእምሮ ጤና እክሎች ካሉብዎ
- ክብደትዎ ከመጠን በላይ ከሆነ
- ነፍሰ ጡር ከሆኑ
- የጤና እንክብካቤ ተደራሽነትዎ ውሱን ከሆነ
በክትባት ተቃዋሚዎች አይታለሉ። የክትባት ተቃዋሚዎች የሚናገሯቸው የተለመዱ ነገሮች:
- "ኤክስፐርቶችን አላምንም"
- "የራሴን ጥናት አድርጌያለሁ።"
- "ክትባቶቹ በጣም ብዙ የጎኒዮሽ የጤና ችግሮች አሏቸው።"
- "በበሽታው መያዝ የበሽታ መከላከያ ስርዓቴን ያጎለብትልኛል። "
- "ክትባቶች መልሰው ሊታመሙ ስለሚችሉ አይሰሩም። "
- "ክትባቶቹ የተዘጋጁት በጣም በችኮላ ነው።"
- "ቫይታሚን ሲ እወስዳለሁ።"
በሳይንስ የሚያምኑ ከሆነ በክትባቶቹም ይተማመኑ። በዚህ ዓመት የ2024 የመኸር ወቅት የCOVID እና የኢንፍሉዌንዛ ክትባቶችን ስለመውሰድ አጥብቀው ያስቡ።
ዶክተር ወይም የጤና መድሕን ዋስትና ያስፈልግዎታል?
- የጤና መድሕን ዋስትና ወይም መደበኛ ዶክተር ከሌለዎ የማህበረሰብ ክሊኒክ ወይም የማህበረሰብ የጤና ስርዓት በጤና ሽፋን ምዝገባ ላይ ሊረዱዎ ይችላሉ።
- ለጤና መድሕን ዋስትና ለመመዝገብ እርዳታ ካስፈለግዎ በ (866) 967-4677 ይደውሉ ወይም ወደ 770 South Bascom Avenue, San José ይሂዱ።
- የሳንታ ክላራ ካውንቲ የማህበረሰብ ክሊኒኮች ለህጻናት መደበኛ ክትባቶችን በነጻ ወይም በአነስተኛ ክፍያ ያቀርባሉ። ክሊኒክ ያግኙ።
ሌላ የCOVID ክትባት የሚያስፈልገኝ ለምንድን ነው?
ወቅታዊ የCOVID ክትባት በነሐሴ 2024 የተፈቀደ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሳንታ ክላራ ካውንቲ ውስጥ እየተሰራጨ ላለው የCOVID ቫይረስ ጥሩ መከላከያ ያቀርባል። ቀደም ሲል በCOVID ተይዘው ወይም ሌሎች ክትባቶችን ወስደው የነበረ ቢሆንም እንኳ ወቅታዊ የCOVID ክትባትን ስለመውሰድ ያስቡ። እያንዳንዱ ዕድሜው ስድስት ወራት እና ከዚያ በላይ የሆነው ሰው የዚህን ዓመት የኢንፍሉዌንዛ ክትባት መውሰድ ይኖርበታል። የዚህን ዓመት የኢንፍሉዌንዛ ክትባት እና ወቅታዊ የCOVID ክትባት በተመሳሳይ የቀጠሮ ጊዜ መውሰድ ችግር አይፈጥርም።
ቀጠሮ ለማስያዝ ዶክተርዎን ዛሬውኑ ያነጋግሩ ወይም በአቅራቢያዎ የሚገኝ የጤና መድን ዋስትናዎን የሚቀበል ክሊኒክ ይፈልጉ። በተወሰኑ ቦታዎች ክትባቶቹን በነጻ ሊያገኙ ይችላሉ።